በጸጥታ ችግር ምክንያት ከሸርቆሌ ወረዳ ከአወልቤጉ ቀበሌ ተፈናቅለው በአሞርማ ፣ጠይባ እና ሸርቆሌ ከተማ ተጠልለው ከሚገኙ ተፈናቃዮች ፣ ከግብረሰናይ ድርጀጅቶች ጋር በመሆን በሸርቆሌ ከተማ ከወረዳ አመራሮች ጋር ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ ፡፡

በቀን 21/11/2013ዓ.ም

በጸጥታ ችግር ምክንያት ከሸርቆሌ ወረዳ ከአወልቤጉ ቀበሌ ተፈናቅለው በአሞርማቀበሌ፣ ፣ጠይባቀበሌ እና ሸርቆሌ ከተማ ተጠልለው ከሚገኙ ከስድስት ሽህ አራትመቶ አንድ በላይ ተፈናቃዮች ፣ እንደሚገኙ ይታወቃል ፡፡ስለሆነም ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት ቀዪ እስኪመለሱ ድረስ ሰባዊ ድጋፍ ለማድረግ እና በቀጣይመልሶ ለማቋቋም ከግብረሰናይ ድርጀጅቶች ጋር በመሆን በሸርቆሌ ከተማ ከወረዳ አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደል፡፡የውይይት መደረኩን የመሩት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ታረቀኝ ታሲሳ እንዳሉት

እንደሚታወቀው እዚህ መጠለያ ከገባችሁ ጊዜ ጀምሮ ኮሚሽኑ መንግስታዊ ከሆኑና መንግስታዊ ከላሆኑ ድረጅቶች ጋር በመሆን ድጋፍ ሲያደረግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ነገር ግን እየተደረገ ያለው ድጋፍ በቂ ባለመሆኑ ዜጎቻችን ችግር ውስጥ ስለሆኑ መንግስት መድረስ ባልቻለባቸው ድጋፍች ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ በማሰብ እናተ ያላችሁበት ቦታ ድረስ የመጣነው ለእናንተ ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግእና ሰላም የሰፈነባቸው ቦታዎች ላይ በመመለስ የመልሶ ማቋቋም ስራ ከግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በጋር በተቀናጀ እና በተደራጀ መንግድ አቅደን ለመስራት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን/ The UN Refugee Agency /UNHCR/ እና አክሽን ፎር ዘኒድ ኢን ኢትዮጵያ /Action for the Need in Ethiopia/፣ Actino plane አሰተባባሪዎችን ይዘን ነው የመጣነው እነሱም ከዚህ ቀደም ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡አሁንም ከእናተጋር በመወያየት የአስቻኳይ ጊዜ ድጋፍ ለማድረግ ለውይይት መጥተዋል ብለዋል ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን/ The UN Refugee Agency /UNHCR/ አሶሳ ማዕከል አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ ቲታ ካን እንደገለጹት ከዚህ በፊት ለከማሽ እና ለመተከል ዞን ተፈናቃዮች ድጋፍ መደረጉን ገልጸው አሁንም ካፕ ውስጥ ተጠልለው ችግር ውስጥ ለሚገኙ እና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አግልግሎት የሚውል ድጋፎችን በማቅረብ አክሽን ፎር ዘኒድ ኢንኢትዮጵያ በኩል እንዲደርስ መደረጉን ገልጸዋ በቅርብም ድጋፍ እንደሚደረግ ተናግረወዋል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ አክሽን ፎር ዘኒድኢን ኢትዮጵያ /Action for the Need In Ethiopia/ አሶሳ ቅርንጫፍ አስተባባሪ የሆኑት አቶ እንዳሉት ከዚህ በፊት በሶስቱም ዞን ተፈናቃዮች በሚገኙበት ካምፕ ድረስ በመንቀሳቀስ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን/The UN Refugee Agency /UNHCR/ ለተፈናቃዮች ያደለውን ድጋፍ ተቋማቸው አብዱልቃድር መሃመድ ከክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስተባባሪነት ለተፈናቃይ የህብረተሰብ ክፍሎች የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ የሚሆኑ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸው በቀጣይም ከሃብት ንብረታቸው እና ከቀየአቸው ተፈናቅለው በካፕ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች በቀጣይም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመሆን መልሶ ማቋቋም ላይ እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የሸርቆሌ ወረዳ ዋና አስተዳደደሪ የሆኑት አቶ አብዱልቃፊር እንዲሪስ እንደገለጹት አብዘኛው ተፈናቃይ በአንድ ማዕከል ያልተሰባሰቡ እና መረጃቻው ከስድስትሽህ አራት መቶ አንደሚበልጥ ገልጸው እየተደረገ ያለው ድጋፍ በምግብ በኩል ችግር ባይኖርም ወቅቱ ክረምት ስለሆነ ከወረዳው የአየር ጸባይ አኳያ መድሃኒት፣አልባሳት፤አጎበር ፣የህጻናት አልሚ ምግብ እና ውሃ ችግር ያለ በመሆኑ ታውቆ ድጋፍ እንዲደረግልን በማለት አሳስበዋል፡፡