የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራሮች እና ሰራተኞች ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ከወር ደመወዛቸው ለመደገፍ እና ደጀን ለመሆን ቃል ገቡ

‹አሶሳ ሐምሌ22/11/201ዓ.ም/ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽ አመራሮች እና ሰራተኞችለሃገር መከላከያ ሠራዊት ከደመወዛቸው ለመደገፍ ቃል ገቡ፡፡

በጉዳዩ ላይ ውይይቱ ላይ ያካሄዱት የኮሚሽኑ ሰራተኞች በሃገር ህልውና ዘመቻ ላይ ለሚገኙት የመከላከያ ሰራዊት እና ለክልሉ ጸጥታ አካላት ከደመወዛቸው ላይ ከ5አስከ50 በመቶ እና ኮሚሽኑ እንደተቋም 20‚000 ብርእና የኮሚሽኑ ኃላፊ የውር ሙሉ ደመወዛቸውን ለመደገፍ እና ደጀን ለመሆን ቃል ገብተዋል፡፡

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ታረቀኝ ታሲሳ እንዳሉት በየደረጃ ያለውን አመራር ፣የመንግስት ሰራተኞች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በሙሉ ያሳተፈ የንቅናቄ ስራዎች በመስራት የሃገራችን አለኝታ የሆኑት የሃገር መከላከያ ሰራዊት እና የጸጥታ ሃይል በገንዘብና በሎጀስቲክ ለማጠናከር ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በካሽ እና በኣይነት እስከ18‚239‚514 ብር ድጋፍ ለማሰባሰብ ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል፡፡ይሁን እንጂ የአሸባሪውን ህውሃት ቡድን ለመደምሰስ ጀግናው የሃገር መከላከያ ሳራዊታችን መስዋት በመክፈል ላይ መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም የተቻለውን ድጋፍ በማድረግ ከሰራዊቱ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የተቋሙ ሰራተኞች በበኩላቸው የሃገራችንን ልዓላዊነት ለማስከበር በህልውና ዘመቻ ላይ ለሚገኙት የመከላከያ ሰራዊት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ በመጥቀስ ከወር ደመወዛቸው ላይ ከ5አስከ50 በመቶ ለመደገፍ እና ደጀን ለመሆን ቃል ገብተዋል፡፡