የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን  ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ታሲሳ ለ2013 አዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ  መልዕክት አስተላለፉ ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን  ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ታሲሳ ለ2013 አዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ  መልዕክት አስተላለፉ ፡፡

በቀን 5 ጷጉሜ/2013ዓ.ም

የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ታሲሳ ለ2014 አዲሱ ዓመት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አቶ ታረቀኝ ታሲሳ ለመላው አገራችንና ክልላችን ህዝቦች እንኳን ለ2014 አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ፡፡አዲሱ ዓመት የሰላም፤የደስታ፤የፍቅር፣ሰርተን የምንበለጽግበት እና ሰላማችን የሚበዛበት ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በክልላችን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በመተግበር የአደጋ ክስተት ክትትል ስራዎችን፤ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማሻሻል፤ የአደጋ ምላሽ እና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን በማቀናጀት በክልሉ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች መከሰት መሠረታዊ መንስኤ የሆኑ ተጽዕኖዎችና ስጋቶች ወደ አደጋነት ከመሸጋገራቸው አስቀድሞ በመከላከል በአደጋ ምክንያት የሚደርስ ጉዳት እንዲቀንስ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ  እንደሚገኝ ተናግረው አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ በአሶሳ ከተማ የሚኙ የደሃ ደሃ ለሆኑ ለ500 ሰዎች በአሉን ተደስተው እንዲያከብሩ ለማድረግ ዘይት፣ስንዴ እና የተለያዩ አልባሳትን ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

 

በ2013 በጀት ዓመት በሶስቱም ዞን እና በአንድ ልዩ ወረዳ ውስጥ በተከሰተ የጸጥታ ችግር አና በተፈጥሮ አደጋ ክስተት ምክንያት 422,371 /አራት መቶ ሃያ ሁለት ሽህ ሶስት መቶ ሰባ አንድ/ ዜጎች የክልሉ መንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ግብረሰናይ ድርጅቶችጋር በመሆን የእለት ዕርዳታ ድጋፍ ዕየተደረገላቸው ሲሆን ከአጠቃላይ የክልሉ ህዝብ ውስጥ 37% የሚሸፍነው ተረጅ ናቸው ብለዋል፡፡

የተከሰተውን የጸጥታ ችግር በመፍታት እና የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ተፈናቃዮችን ወደ ነበሩበት ቀዪ እስኪመለሱ ድረስ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚደረግ እና የመልሶ ማቋቋም ስራም እንደሚከናወን  በመግለጽ ሃገራችን ኢትዮጵያ ከተያያዘችው የብልጽግና የለውጥ ጉዞ እና የተጀመሩ የልማት ፕርጀክት ስራዎችን በማጠናቀቅ እና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመስራት ለህዝባችን ሁለንተናዊ  ተጠቃሚነት ተግተን የምንሰራ ይሆናል መንግስት የጀመረውን ስራ በዘላቂነት ለማስቀጠል መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ባለሃብቶች ፣ሞዴል አርሶ አደሮች ፣የከተማው ህዝብ ፣በጎ አድራጎት ማህበራት ይህን አስቸጋሪ እና ፈታኝ ወቅት ለመሻገር ከጎናቸው በመሰለፍ ላበረከቱት ሁሉን አቀፍ ድግፍ  በማመስግን በቀጣይም ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል  ጠሪ አቅርበዋል፡፡

አክለውም በዓለም አቀፍ ደረጃ በወረርሽኝ መልክ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ በሽታ እንደሃገር እና እንደ ክልል ከፍተኛ የሆነ ተጽዕኖ በህዝብ እና በመንግስት ላይ መፍጠሩን በማስታወስ የችግሩን አሳሳቢነት ግምት ውስጥ በማስገባት እና በሽታው ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ለመካላከል እና  ማህበረሰቡ ላይ  የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ለመቆጣጠር እንዲቻል የክልሉ መንግስት እና ተቋሙ ዘርፈ-ብዙ ጥረቶች በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም አዲሱ ዓመት የሰላም ፣ የደስታ፣ የፍቅር ፣ የመቻቻል እና የብልጽግና ዘመን እንዲሆን በመመኘት ህብረተሰቡ በዓሉን በሚያከብርበት ወቅት ከኃይማኖት አባቶቸች እና ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ምክረ-ሀሳቦች በመተግበር የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ በማሳሰብ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

መልካም ዓዲስ ዓመት !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *