በቀን 20/11/2013ዓ.ም ከአሶሳ ዞን ከቢልድግሉ ወረዳ ከሸርቆሌ ወረዳ ተፈናቅለው እና ከኦሮሚያ ክልል ከአይራ ጉሊሶ፣ከባቦ ገምቤል፣ ከመንዲ ወረዳ እና ከከማሽ ዞን ሴዳል ወረዳ ተፈናቅለው ባምባሲ ወረዳ ለሚገኙ ተፈናቃዮች አስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ድጋፋ ከሶስቱም ወረዳ አመራሮች ጋር በአሶሳ ከተማ ውይይት በማድረግ ርክክብ አድርገዋል፡፡በውይይት መደረኩ ላይ ውይይቱን የመሩት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ታረቀኝ ታሲሳ እንዳሉት ለሶስቱም ወረዳ በጊዜአዊ በመጠለያ ካፕ ውስጥ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ኮሚሽኑ ከቤሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን እና ከግብረሰ ናይ ድርጅቶች የሚገኙ ድጋፎችን ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸው፡፡ነገርግን የሚደረጉ ድጋፎች በቂ ስላልሆኑና የቢልድግሉ ወረዳው የተፈናቃዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ እርዳታው ተጠናክሮ መቀጠል ስለአለበት ከሚመለከታቸው ወረዳ አመራሮች ጋር በመወያየት ድጋፉ እንዴት መቀጠል እንዳለበት እና ወቅቱ ክረምት ስለሆነ ህዝባችን በብርድና እና በበሽታ እየተጎዳ እኛ በተመቻቸ ሁኔታ የምንኖርበት ሁኔታ መኖር የለበትም በማለት የክልሉ መንግስት በድጎማ ባጀት የተገዙትን አልባሳት እና እህሎች ድጋፍ ለማድረግ አላማ ያለው የውይይት መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የተደረጉ ድጋፍም ባምባሲ ወረዳ ላይ 3872 ተፈናቃይዮች ያሉ ሲሆን ከዚህ በፊት ድጋፍ የተደረገ ስለሆነ ለአሁኑ 300 ብርድልብስ ለወረዳው ም/ አስተዳደዳሪ ለሆኑት ለአቶ አብዱልከሪም አብዱላሂ በማስረከብ በቀጣይም ከኦሮሚያ መንግስት ጋር በመጋገገር ወደነበሩበት ቀዪ በመመለስ የመልሶ ማቋቋም ስራ ለመስራት እየተሰራ እንደሆነ ተናጋረዋል፡፡
ለቢልድግሉ ወረዳ ህዝቡ ከተፈናቀለ ጊዜ ጀምሮ ከቤሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን፣ ከአሶሳ ዩንርሲቲ፣ከቀይ መስቀል ማህበር እና ከክልሉ መንግስት ጋር በመሆን የተገኙ ድጋፎችን ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ነገርግን በወረዳው የተፈናቃዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ እርዳታው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በማሳሰብ በዛሬው እለት 8 ድንካኖች እና 500 ኩንታል ስንዴ ለወረዳው ዋና አስታዳሪ ለሆኑት ለአቶ ባበከር አብዱላሂ አስረክበዋል፡፡
ለሸርቆሌ ወረዳ /ስድስት ሽህ አራት መቶ አንድ / ተፈናቃዮች በካምፕ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ለነዚህ ተፈናቃዮች ድጋፍ ሲደረግ መቆየትን ገልጸው ተፈናቃዮችን ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሳራ እንደሆነ በመግለጽ በዛሬው እለት 1500 ብርድልብስ ፣ 20 ባለ50 ሜትር ሸራ እና 200 ኩንታል ሰንዴ ለወረዳው አስተዳዳሪ ለሆኑት ለአቶ አብዱልቃፊር እንዲሪስ አስረክበዋል፡፡