አሶሳ ሐምሌ29/11/201ዓ.ም/ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽ የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምግማ እና የውይይት መድረክ ከመላ ሰራተኞች ጋር አካሄዶአል፡፡ በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ታረቀኝ ታሲሳ እንዳሉት ኮሚሽኑ በክልሉ ለተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች መከሰት መሠረታዊ መንስኤ የሆኑ ተጽዕኖዎችና ስጋቶች ወደ አደጋነት ከመሸጋገራቸው አስቀድሞ በመከላከል በአደጋ ምክንያት የሚደርስ ጉዳት እንዲቀንስ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በበጀት ዓመቱም ለአደጋ ተጎጂዎች የእለት እርዳታ አቅርቦትን እና የመልሶ-ማቋቋም ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ይህንን ስራ ለማከናወን የክልሉ መንግስት እና ባለድርሻአካላት ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር በመግለጽ ላደረጉት ተሳትፎም አመስግነዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የበጀት ዓመቱ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶአል፡፡
በመጨረሻም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ እየተሻለ ውጤት ለአስመዘገቡ ሰራተኞች እና ለብዙ ዓመታት መ/ቤቱን ሲያገለግሉ የነበሩ እና ጡረታ ለወጡ ሰራተኞች የእውቅናና የማትጊያ ሽልማት በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡