አሶሳ ፣ነሃሴ 19፣2013ዓ.ም በከማሽ ዞን ሴዳል ወረዳ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ለተፈናቀሉ 27‚500 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የአስቸኳይ ጊዜ ሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ
መደረጉን የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ተወካይ እና የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እና መልሶ ማቋቋም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አስረሳኸኝ አበጀ እንደገለጹት የወረዳው አመራሮችእና ካቢኒዎች የተፈናቃዮችን ቁጥር ባሳወቀን መሰረት ከብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የተላከውን ምግብ ነክ እና ምግብነክ ያልሆኑ ድጋፎች ለወረዳው አመራሮች አስረክበናል ብለዋል ፡፡
የተደረጉ ድጋፎችም 600 ኩንታል ስንዴ፣10 ቦንዳ /ፎዴ/ የህጻናት እና የአዋቂዎች አልባሳት፣2‚000 ሊትር ዘይት እና 10 ኩንታል ስንዴ ሲሆን ድጋፉን ለተፈናቃዮች ለማድረስ ከሴዳል ወረዳ አመራሮች ጋር በመወያየት ተሸከርካሪ እና የትራንስፖረት ወጭ በጋራ በመሸፈን በአሶሳ ከተማ ላይ ውርዶ የቆየውን ድጋፍ ለወረዳው ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ ለሆኑት ለአቶ ባቆፍ ፍላቴ ርክክብ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ሰባአዊ ድጋፍ ማድረግ ማለት ከየትኛውም ፖለቲካ ነጻ ሲሆን ሰው ለሆነ ሁሉ ድጋፍ መደረግ ስለአለብት እና በምግብ እጥረት የትኛውም ሰው መሞት ስለሌለበት ለተፈናቃዮች በ72 ሰዓት ለመድረስ ባለድርሻ አካላት ትብብር ማድግ አለባቸው ሲሉ አቶ አስረሳኸኝ አበጀ ጥሪዓቸውን አስተላልፈዋል፡፡